# ODAA WALLOO
# ካረ ከሎ ኦዳ/ ODA KAARRA KALO ******************************* የኦዳ ካረ ከሎ ጉዳይ ይህ የምትመለከቱት ጉዙፍ እና ታሪካዊ ኦዳ (ዋርካ) በወሎ ከሚሴ በዋናው አስፖልት በትልቁ መስጊድ እና በኦሲስ ሆቴል መካከል ባለው ቅያስ መንገድ "#ካረ_ከሎ" ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ይገኛል። በከሚሴ ከተማ ይህንን መሰል ታሪካዊ ኦዳዎች ያሉ ሲሆን ለአብነትም ሐሙስ ገበያ ቅቤ ተራ፣ ሰዳሳ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ፣ እንዲሁም በእንክብካቤ ጉድለት በቅርብ ጊዜ ደርቆ የጠፋው ጫት ተራ የነበረው ኦዳ ይጠቀሳሉ ። በነገራችን ላይ ጫት ተራ በነበረው ኦዳ ላይ ነበር አጼ ሐይለስላሴ ጀግናውን የኦሮሞ ታጋይና መሪ " ሐሰን አሜ ዘራፋን በግፍ ሰቅሎ የገደለው ። "#ኦዳ_ገራዶ"ን ጨምሮ ሁሉም ከወሎ ኦሮሞዎች ጋር በተያያዘ ታሪክ አላቸው ። ለወደፊት ስለ ሁሉም ሰፋ ያለ ጹሁፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ ። አሁን ግን ወደ ዋናው አጀንዳዬ ልመለስ። ከታች በምስሉ ላይ የምታዩት ኦዳ ጥንት የወሎ ኦሮሞዎች ተሰባስበው የሚመክሩበት ፣የተጣላ የሚታረቅበት፣ ያጠፋ በነበረው ህግ መሰረት የሚቀጣበት፣ ድርቅ ሲከሰት ወዳጃ ተቀምጠው ዱአ የሚደረግበት የህዝብ መገናኛ (ፖርላማ) ነበር ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለህዝብ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ትዝታ ነው።ከ27 አመት በፊት መስጊዱ ሲከለል በርካቶች ኦዳው እንዲካተት ጠይቀው ነበር። ምክንያቱም ከኦዳው ጎን የሙስሊሞች ቀብር ስለነበር ። የሆነው ሇኖ ይህንን ታሪካዊ ቦታ በልማት ስም ድራሹን ለማጥፍት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል። አንዳንዶችም በድፍረት የኛ ነው ይገባናል መንግስት ሰጥቶናል በማለት በዘመዶቻቸው በኩል ያሰሩትን ወረቀት በመያዝ ጠበቃ ይዘው ሲሟገቱ ታይተ...
Comments
Post a Comment