# ODAA WALLOO

  # ካረ ከሎ ኦዳ/ ODA KAARRA KALO
*******************************
የኦዳ ካረ ከሎ ጉዳይ
ይህ የምትመለከቱት ጉዙፍ እና ታሪካዊ ኦዳ (ዋርካ) በወሎ ከሚሴ በዋናው አስፖልት በትልቁ መስጊድ እና በኦሲስ ሆቴል መካከል ባለው ቅያስ መንገድ 

"#ካረ_ከሎ" ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ይገኛል። በከሚሴ ከተማ ይህንን መሰል ታሪካዊ ኦዳዎች ያሉ ሲሆን ለአብነትም ሐሙስ ገበያ ቅቤ ተራ፣ ሰዳሳ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ፣ እንዲሁም በእንክብካቤ ጉድለት በቅርብ ጊዜ ደርቆ የጠፋው ጫት ተራ የነበረው ኦዳ ይጠቀሳሉ ። በነገራችን ላይ ጫት ተራ በነበረው ኦዳ ላይ ነበር አጼ ሐይለስላሴ ጀግናውን የኦሮሞ ታጋይና መሪ " ሐሰን አሜ ዘራፋን በግፍ ሰቅሎ የገደለው ።

"#ኦዳ_ገራዶ"ን ጨምሮ ሁሉም ከወሎ ኦሮሞዎች ጋር በተያያዘ ታሪክ አላቸው ። ለወደፊት ስለ ሁሉም ሰፋ ያለ ጹሁፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ ። አሁን ግን ወደ ዋናው አጀንዳዬ ልመለስ። ከታች በምስሉ ላይ የምታዩት ኦዳ ጥንት የወሎ ኦሮሞዎች ተሰባስበው የሚመክሩበት ፣የተጣላ የሚታረቅበት፣ ያጠፋ በነበረው ህግ መሰረት የሚቀጣበት፣ ድርቅ ሲከሰት ወዳጃ ተቀምጠው ዱአ የሚደረግበት የህዝብ መገናኛ (ፖርላማ) ነበር ።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለህዝብ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው ትዝታ ነው።ከ27 አመት በፊት መስጊዱ ሲከለል በርካቶች ኦዳው እንዲካተት ጠይቀው ነበር። ምክንያቱም ከኦዳው ጎን የሙስሊሞች ቀብር ስለነበር ። የሆነው ሇኖ ይህንን ታሪካዊ ቦታ በልማት ስም ድራሹን ለማጥፍት የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል። አንዳንዶችም በድፍረት የኛ ነው ይገባናል መንግስት ሰጥቶናል በማለት በዘመዶቻቸው በኩል ያሰሩትን ወረቀት በመያዝ ጠበቃ ይዘው ሲሟገቱ ታይተዋል።

ህዝቡም እየተሰራበት ያለውን አሻጥር ዝም ብሎ አልተመለከተም ጉዳዩን ለሚመለከተው አካል ከማሳወቁም በላይ ጉዳዪን እዲከታተል አምጦ ለወለደው ድርጅት (#ወልዳ_ሚሶመ_ኦሮሞ_ወሎ) አላፊነቱን ባደራ ጭምር ሰጠ። ድርጅቱም በህግ አግባብ ወራሪዎቹን ለማስቆም ይቻል ዘንድ የሚያስፈልገውን የታሪክ ሰነድ በማቅረብ ሞግቷል። በተደረገው ክርክርም ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን አለኝ የሚለውን ማስረጀ ከመረመረ ቦሃላ አግባብ እንዳል ነበር ከመረጋገጡም በላይ የቦታውን ቀደምት ታሪክ ለመጠበቅ፣ የቅድመ አያቶችን አሻራ ለማቆየት የህዝቡም ሀብት በመሆኑም ጫምር ፍርድ ቤቱ ለድርጅቱ ወስኖ አስረክቧል።

ወልዳ ሚሶማ ኦሮሞ ወሎ ኦዳውን በህግ አግባብ ለህዝብ ካስመለሰ ቦሃላ የኦሮሞ የባህል ቁሳቁሶች ማሳያ እና የባህል አልባሳት መሸጫ ህንፃ ከጀርባው ለማስገንባት ኦዳውም ታሪካዊነቱን ይዞ እንዲቀጥል እንክብካቤና ጥበቃ ለማድረግ ወስኖ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሮ ነበር። ለግንባታ የሚሆን ድንጋይም በቦታው ላይ አስቀምጠል። በዚህ ሁኔታላይ እያለ በሴሮኞች ድርጅቱ እንደፈለገው መንቀሳቀስ እንዳይችል ተደረገ። ለምን ለሚለው በስፍት እነግራቹሀለው ጠብቁ።

ወልዳው ሊያሳካ ካቀደው በርካታ ኘሮጀክቶች መካከል የ #ኦዳ_ከረ_ከሎ ግንባታ አንዱ ነው። 

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

# Hortee ka,umsa oromoo

#Jamaa Negus(muhammad shaafii ibn muhammad xaahir)